Goolgule
Ethiopian News
- Website
- goolgule.com · all feeds from this site
- Feed URL
https://www.goolgule.com/feed/
Read it in your FeedListing reader
Or add to: Feedly Inoreader Raw feed
Latest posts
-
ኢትዮጵያ በሰማይ ላይ ነዳጅ የሚሞሉ የኢሉሺን (Il-78) አውሮፕላኖችን ከሩሲያ ልትገዛ ነው
ኢትዮጵያ የአየር ኃይሏን የመዋጋት አቅም በከፍተኛ ደረጃ ከሚያሳድጉ እና የቀጠናውን የኃይል ሚዛን ቀያሪ ከተባሉት ዘመናዊ የጦር ጀቶች በተጨማሪ 2 የኢሉሺን (Ilyushin Il-78) የአየር ላይ ነዳጅ መሙያ ጫኝ አውሮፕላኖችን ለመግዛት ከሩሲያ ጋር ስምምነት መፈራረሟን ወታደራዊ መረጃ ተንታኞች ገለጹ። ይህ ግዢ በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይፋ ካደረጉት የ12 ሱኮይ (Sukhoi Su-35) ዘመናዊ የውጊያ ጄቶች ግዢ ጋር በቀጥታ…
-
ካይሮ ያጣችውን የሩሲያ ጄቶች አዲስ አበባ የታጠቀችበት ምሥጢር
የግብፅ ቁጭት እና የኢትዮጵያ ስኬት የኢትዮጵያ አየር ኃይል በጥራት ፍጹም የአየር የበላይነት በአፍሪካ ተቀዳጅቷል ግብጻውያን የሚዲያ ተቋማት እና የክልሉ የፖለቲካ ታዛቢዎች ኢትዮጵያ 12 ዘመናዊ የሩሲያ Su-35 የጦር ጄቶችን እና የ S-400 የየብስ-ወደ-አየር ፀረ-አውሮፕላን ሚሳኤል መከላከያ ስርዓትን መታጠቋን በከፍተኛ ስትራቴጂካዊ ስጋት እየተከታተሉት ይገኛሉ። ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ማሳያ፣ ወደ አዲስ አበባ የገቡት የጦር ጄቶች ላይ…
-
ኢትዮጵያ ሱ-35 ተዋጊ ጄቶች እና የኤስ-400 ዘመናዊ የአየር መከላከያ ስርአት በመታጠቅ ከሰሃራ በታች ብቸኛዋ ሀገር ሆናለች
የቀጣናውን የኃይል ሚዛን የቀየረው የኢትዮጵያ ወታደራዊ ግዥ የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይልን የአየር ላይ የመከላከል እና የማጥቃት አቅም በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ የተነደፈውን ስትራቴጂ ተከትሎ፣ አገሪቱ 12 የሩሲያ ሰራሽ ሱ-35 (Su-35 4++ Generation) ተዋጊ ጄቶችን እንዲሁም የአገሪቱን ሰማይ በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ የሚያስችሉ 4 የኤስ-400 (S-400 Missile Batteries) የረጅም ርቀት የአየር መከላከያ ስርአቶችን…
-
ሻዕቢያ ኢትዮጵያን በ“ካሚካዜ” ድሮኖች ለመምታትና በዘር ግጭት ለማፍረስ ሰፊ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተሰማ
የሻዕቢያ ቡድን የኢትዮጵያን ሰላምና ደኅንነት በሁሉም አቅጣጫዎች ለማደፍረስና ሀገሪቱን ለማፍረስ ቀንና ሌሊት ሙሉ አቅሙን አሰባስቦ እየሠራ መሆኑን የሚያጋልጥ ሚስጢራዊ መረጃ ለጎልጉል ደርሷል። ለድረ-ገጻችን የደረሰው ይኸው መረጃ እንደሚያመላክተው፣ የሻዕቢያ መዋቅር በውጭ አገር ከሚገኙ ደጋፊዎቹ ጀምሮ በአገር ውስጥ እስከሚዘረጉ የስለላ መረቦች ድረስ ሰፊ ስምሪት በመስጠት ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል። ለጎልጉል የደረሰው መረጃ የሴራውን…
-
ጆን መዲድ “ቀዝኖ እና ልብሱ ተበላሽቶ” ነው መከላከያ የማረከው
* የመከላከያ ሠራዊት አባላት አጽድተው ነው ለፎቶ ያበቁት * ስለ ጆን መዲድ መማረክ ከግንባር የተገኘ መረጃ ዮሐንስ ወልደጊዮርጊስ ወይም በበረሃ የቅንጦት ስሙ ጆን መዲድ፣ ሲማረክ በድንጋጤ “ቀዝኖ እና ልብሱ ተበላሽቶ” እንደነበር ጎልጉል ከግንባር የደረሰው መረጃ ያስረዳል። በዚህ የተበላሸ ሁኔታ ለሰው እንዲታይ ያልፈቀደው በጽኑ ወታደራዊ ዲሲፒሊን የሚመራው የመከላከያ ሠራዊት ለፎቶ ከመቅረቡ በፊት ልብስ እንዳስቀየረው የትግራይ የሰላም […]
-
በጆን መዲድ መማረክ አደረጃጀቱ እየተፈረካከሰ በመሆኑ እነ ወዲ እምበይተይ፣ ምግበይ፣ ቀጣዮች ሊሆኑ ይችላሉ
ከትህነግ (ህወሃት) ታጣቂዎች ከመቐሌ መውጣት በኋላ በምስጢር ተዋቅሮ የነበረው አዲሱ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ዕዝ (ሴንተራል ኮማንድ) እየፈረሰ መሆኑ ተነገረ። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የዚሁ ድብቅ የጦር መዋቅር ቁልፍ መሪ የነበረው ታጋይ ዮሐንስ ወልደጊዮርጊስ (ጆን መዲድ) የመፈራረሱ ዋና ምክንያት የጆን መዲድ መማረክ ሲሆን እርሱም ከምርኮ በኋላ ትናንት ከአክሱም ተነስቶ አዲስ አበባ መግባቱ ታውቋል። ሌሎችም አዛዦች እንዲሁ ይማረካሉ […]
-
ከታክስ ስወራ እስከ ሐሰተኛ ጋብቻ፦ በኢትዮጵያ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊ ዳያስፖራዎችን ለማደን የተዘረጋው አዲሱ የአሜሪካ መረብ
በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ቡድኖችን (ትህነግ፣ ፋኖ፣ ኦነግ-ኦነሠ እና ሌሎችንም) በገንዘብ፣ በማኅበራዊ ሚዲያና በተለያዩ መንገዶች የሚደግፉ የዲያስፖራ አባላት ላይ ከባድ የሕግና የኢሚግሬሽን ስጋት መደቀኑን የጎልጉል ምንጮች አስጠነቀቁ። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በቅርቡ በሰጡት መግለጫ፣ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ የጦር መሣሪያ ያነሱትንና በቅርቡ ጥምረት የፈጠሩትን የታጠቁ ቡድኖች እንቅስቃሴ “የመገንጠል እና…
-
ኔታንያሁ የሶማሊላንድን ሉዓላዊነት ያረጋገጠ አዲስ ቀጣናዊ ካርታ ይፋ አደረጉ
* ውሳኔው የኢትዮጵያን የወደብ ፖለቲካ ስትራቴጂካዊ ኃይል ሰጥቶታል የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ እሑድ ጥቅምት 8 ቀን 2019 ዓ.ም. ባቀረቡት አዲስ ብሔራዊ የደኅንነት ዶክትሪን መግለጫ ላይ፥ ሶማሊላንድን ከቀሪዋ ሶማሊያ ነጥሎ ሉዓላዊት ሀገር አድርጎ የሚያሳይ አዲስ ጂኦ-ፖለቲካዊ ካርታ ይፋ አድርገዋል። ይህ እርምጃ ቀጣናዊ የኃይል ሚዛኑን በእጅጉ የሚቀይር ሲሆን፥ በተለይም ኢትዮጵያ በሶማሊላንድ በኩል የባሕር በር…
-
ትውልደ ሶማሊያዊቷ ናፊሳ በተዘቀዘቀ የአሜሪካ ሠንደቅ ፊት በሶማሊኛ ምርጫ ቅስቀሳ ማድረጓ ቁጣ ቀሰቀሰ
በኦሬገን ግዛት ጠቅላይ ግዛት የዋሺንግተን አውራጃ ኮሚሽነር ሆና ለመመረጥ የምርጫ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ የምትገኘው ትውልደ ሶማሊያዊቷ ናፊሳ ፋይ፣ በሚኒሶታ ግዛት ውስጥ ባደረገችው የቅስቀሳ መድረክ ላይ በተዘቀዘቀ የአሜሪካ ሠንደቅ ፊት ሙሉ ንግግሯን በሶማሊኛ ቋንቋ ብቻ በማድረጓ በአሜሪካ ከፍተኛ ቁጣንና ውዝግብን ቀስቅሳለች። ይህ ድርጊት በአሁኑ ወቅት የዜግነት ስረዛ ምርመራ እየተካሄደባት ከምትገኘው ሌላኛዋ ትውልደ ሶማሊያዊ የኮንግረስ…
-
በአሜሪካ የሚገኙ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊዎች ላይ የተደቀነው አዲስ ስጋት
* ውሳኔው ከዜግነት መነጠቅ እስከ ከአገር ማባረር ይደርሳል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፣ በ“ሽብርተኝነት እና በመገንጠል” ተግባር ላይ የተሰማሩ ትህነግ፣ ኦነግ ሸኔ፣ ፋኖ እና ሌሎችንም ያካተተውን የትብብር ለሕልውና ታጣቂ ቡድኖች ስብስብ አስመልክቶ ካስተላለፉት ጠንከር ያለ መልእክት በመቀጠል፣ ዋሽንግተን እነዚህን ቡድኖች በሚደግፉ አካላት ላይ የማያወላዳ እርምጃ መውሰድ እንደምትጀምር ጎልጉል ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ያገኘው…